Zinash

Zinash አቤቱ እንደ ቸርነት መጠን ማረኝ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተ?

05/07/2026
14/06/2026

"የነጭ ልብሴ አቅም ያበቃበት ቦታ"

እኔ ዶ/ር የሮም ጌታቸው እባላለሁ። ከ6 ዓመታት በላይ በሕክምና ሙያ ውስጥ ሰርቻለሁ። በየቀኑ የታመሙ ሰዎችን አክሜያለሁ፣ ለብዙ ቤተሰቦች ተስፋ ሆኜያለሁ፣ ሕይወት ለማዳን በቻልኩት ሁሉ ተግቻለሁ።

ዛሬ ግን ልጄን ለማዳን እኔ ራሴ የሰዎችን እገዛ የምሻበት ወቅት ላይ እገኛለሁ።

የ3 ዓመት ተኩል ልጄ በአጥንት ካንሰር ተጠቅቷል። ገና ሕይወትን መረዳት ያልጀመረ፣ ሕልሙን መናገር ያልቻለ፣ በእናቱና በአባቱ እቅፍ ውስጥ መጫወት የሚገባው ሕፃን ዛሬ የካንሰር ሕመምና የኬሞቴራፒ ስቃይ እየተሸከመ ነው።

እንደ አባት ይህን ማየት ያማል። እንደ ሐኪም ደግሞ የበለጠ ያማል። ምክንያቱም ልጄ የሚያስፈልገውን የላቀ ሕክምና በሀገራችን ውስጥ ማግኘት አልቻለም።

ለዓመታት በጤና ሥርዓቱ ውስጥ የሰራሁ ሰው እንደመሆኔ አንድ ሀቅ ልናገር። የሀገራችን የጤና ሥርዓት አሁንም ለእንደዚህ ያሉ ውስብስብ በሽታዎች በቂ አቅም የለውም።

ብዙ ሕፃናትና ቤተሰቦች የመጨረሻ ተስፋቸውን ከሀገር ውጭ ባሉ ሆስፒታሎች ላይ እንዲጥሉ ይገደዳሉ።

የበለጠ የሚያሳዝነው ደግሞ ሕይወት ለማዳን የሚሰሩ ሐኪሞችና የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከእንዲህ ያሉ ከባድ የጤና ቀውሶች ለመታደግ በቂ የገንዘብ አቅም እንዳይኖራቸው የሚያደርግ እውነታ ነው። ለሌሎች ሕይወት የሚታገሉ ሰዎች ራሳቸው ሲፈተኑ የሚደግፋቸው ሥርዓት የለም።

ዛሬ ልጄን ለማዳን እና ወደ ውጭ ሀገር ለሚደረገው ሕክምና ለማድረስ 3.5 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልገናል። ይህ ገንዘብ ከቤተሰባችን አቅም በላይ ነው።

ከዚህም በላይ የሚያስጨንቀን ጊዜው ነው። ሐኪሞቹ የሰጡን ጊዜ አንድ ወር ተኩል ብቻ ነው። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ሕክምናውን መጀመር ካልቻልን የልጄ የመዳን እድል በእጅጉ ይቀንሳል።

ስለዚህ ይህን መልዕክት እንደ ሐኪም አይደለም የምጽፈው፤ ልጁን ለማጣት የሚፈራ አባት ሆኜ ነው።

እባካችሁ የምትችሉትን ያህል ድጋፍ አድርጉ።
መልዕክቱን ለሌሎች አጋሩ።
ለልጄ ጸልዩ።

CBE - 1000149557982
Abay - 2091011011819814
Awash : 013201344371300
Tele birr: 0910119336

GoFundMe: https://www.gofundme.com/f/help-tsegabe-fight-cancer?lang=en_US&ts=1780047340

ለእናንተ ትንሽ የሚመስለው እርዳታ ለልጄ የመኖር እድል ሊሆን ይችላል። #ሼር በማደረግና በማጋራት እንድታግዙኝ በፈጣሪ ስም እለምናችኋለሁ ።

Via፦ ዶ/ር የሮም ጌታቸው

ግዮን ማለዳ

Address

Addis Ababa
2121

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zinash posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Hotel

Send a message to Zinash:

Shortcuts

Share