05/11/2026
የሀዘን መግለጫ
በፕላቲኒየም ሆቴል የጥበቃ (Security) ክፍል በማገልገል ላይ የነበሩት ውድ የሥራ ባልደረባችን ወ/ሮ ትግስት ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው የፕላቲኒየም ሆቴል ማኔጅመንትና ሠራተኞች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን።
ወ/ሮ ትግስት በሆቴላችን በነበራቸው የሥራ ቆይታ በትጋት ና በሀላፊነት በማገልገል ለድርጅታችን የጎላ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
በዚህ አስቸጋሪና አሳዛኝ ወቅት ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ጓደኞቻቸው ከልብ የመነጨ መጽናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪም በዚህ ከባድ የሀዘን ጊዜ ብርታትና መጽናናትን ይስጣቸው።
ሁሌም በፕላቲኒየም ቤተሰቦቻችን ልብ ውስጥ ይኖራሉ!
ከፕላቲኒየም ሆቴል ማኔጅመንትና ሠራተኞች